በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዛሬ 15 ዓመት አፍሪካ ከራሷ ተርፋ ዓለምን ትመግባለች ሲሉ ኢፋድ ፕሬዚዳንት ተነበዩ


የዓለምአቀፉ የግብርና ልማት ድርጅት - ኢፋድ ፕሬዚዳንት ካናዮ ንዋንዜ ይህንን አስተያየታቸውን የሰጡት ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በተካሄደው የስምንቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሃገሮች ስብሰባና በውጤቱ ላይ አተኩረው በቅርቡ በኢንተርኔት ባሄዱት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

በግንቦት አጋማሽ አካባቢ ዋሽንግተን ዲ.ሲ ላይ የተካሄደው የስምንቱ ከበርቴ ሃገሮች ስብሰባ መሪ አጀንዳ ልማትና የምግብ ዋስትና እንደነበሩ ይታወሣል፡፡

የዛሬ ሦስት ዓመት የጣልያኗ ላክዊላ ከተማ ላይ አካሃዶት የነበረውን ጉባዔውን ሲያጠናቅቅ ጂ ስምንት ባወጣው የጋራ መግለጫው ለተራዘመ ጊዜ በግብርናና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በቂ መዋዕለ ነዋይ አለመፍሰሱና አጥጋቢ ሥራም አለመሠራቱ በወቅቱ ከተፈጠረው የምግብ ዋጋ ቀውስ እና ከዓለም አጠቃላይ የምጣኔ ሃብት ውድቀት ጋር ተዳምረው በማደግ ላይ ባሉ ሃገሮች ውስጥ ድህነቱ እንዲባባስ፣ ረሃቡም እንዲበረታ ማድረጋቸውን ገልፀው ነበር፡፡

መቶ ሚሊየን ሰው ወደ ድህነትና የረሃብ አዘቅት እንዲገባ ተገድዷል፡፡ አውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም እንዲደረስባቸው በዕቅድ ተይዘው፣ ተስፋም ተጥሎባቸው የነበሩ የሚሌንየሙ የልማት ግቦችም ለአደጋ ተጋለጡ፡፡

በረሃብና በድህነት ምክንያት በዓለም ዙሪያ ለብዙ ጉስቁልና የተዳረገው ሰው ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን ዘልቆ ተረፈ፡፡

በመሆኑም ላኩላ ላይ የተሰባሰቡት የከበሩ ሃገሮች መሪዎች የሰውን ልጅ ከረሃብና ከድህነት ነፃ ማውጣት ይቻል ዘንድ ቆፍጣናና አጣዳፊ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አስተዋሉ፡፡

በመሆኙም ምግብና የምግብ ዋስትና፣ እንዲሁም ዘላቂ የግብርና ልማት የፖለቲካው ቅድሚያ መሆን ይገባቸዋል ሲሉ አወጁ፡፡

ሐምሌ 3 ቀን 2001 (ልክ የዛሬ ሦስት ዓመት ማለት ነው) ፅፈው በፈረሙትና ለዓለምም ባወጁት ባለ12 ነጥብ መግለጫቸው ላይ ሃያ ሁለት ቢሊየን ዶላር በመጭዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ ለማዋጣትና ረሃብና ድህነትን በተባባረ ክንድ ለመውጋት መወሰናቸውን አስታወቁ፡፡

ከሦስት ዓመት በኋላ ግንቦት 10 እና 11 / 2004 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲ.ሲ ላይ የተጠራው የጂ ስምንት የዘላቂ ልማትና የምግብ ዋስትና ጉባዔ የላክዊላውን መግለጫና የተገቡ ቃሎች ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገምግሞ አዲስ ዕቅድና ዘመቻ ጀምሯል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)

XS
SM
MD
LG