በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ጉዳይ


የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:50 0:00

የኢትዮጵያ መንግሥት ለነዳጅ የሚያደርገውን ድጎማ ደረጃ በደረጃ የማንሳቱን እርምጃ ቀጥሏል።

በያዝነው ሳምንት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በአንዳንድ የነዳጅ ውጤቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል። ጭማሪው ግን “ለህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን አይመለከትም” ብሏል።

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች በበኩላቸው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን ተከትሎ ሊጨምር የሚችለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል።

መንግስት የነዳጅ ድጎማውን ደረጃ በደረጃ እያነሳ ያለው ለድጎማ የሚያወጣው በቢሊዮን የሚሰላ ገንዘብ በሌሎች ሥራዎች ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ስለሆነ ነው ይላል።

XS
SM
MD
LG