No media source currently available
አሥር የተለያዩ ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ከትናንት በስተያ ዓርብ፣ ጥር 5 እና ቅዳሜ ጥር 6 ጉባዔ አካሂደዋል። ጉባዔው የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ በሚባሉ ሦስት ድርጅቶች መሆኑን አስተባባሪዎቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል።