በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ተስፋ እና ፈተና


የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ተስፋ እና ፈተና
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:58 0:00

ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ልማት ላይ ከፍተኛ መሻሻል ለማስመዝገብ ያቀደች መሆኗን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ሰሞኑን በአንድ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ተናግረዋል። የኢንዱስትሪ ዘርፍ በኢትዮጵያ ያለው የኢኮኖሚያዊ ሚና ከአጠቃላይ ሃገራዊ ሃብቱ 6.8 በመቶውን እንደሚሸፍን ገልፀው ይሄንን ወደ 17.2 በመቶ ለማሳደግ እንደሚሠራም ተናግረዋል።

“የኢንዱስትሪው ዘርፍ በርካታ እንቅፋቶች እና ተስፋዎች አሉት” ያሉት ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል በተካሄደ ንቅናቄ በሀገሪቱ ያሉ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙበትን ይዞታ ለመፈተሽ ጥረት መደረጉን ገልፀዋል። ባለፉት አስርት ዓመታት 446 ኢንዱስትሪዎች ሥራ ማቆማቸውም በስብሰባው ላይ ተገልጿል። የንግድና ምጣኔ ባለሞያው ፕሮፌሰር መንግሥቱ ከተማ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ብዙ ችግሮች የተጋረጡበት እንደሆነ ይናገራሉ።

/በዚህ ዙሪያ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG