በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሰመኮ ከተመድ ቡድን ጋራ ያወጣው የምርመራ ሪፖርት “ለሽግግር ፍትሕ መነሻ ይኾናል” ሲል ሞገተ


ኢሰመኮ ከተመድ ቡድን ጋራ ያወጣው የምርመራ ሪፖርት “ለሽግግር ፍትሕ መነሻ ይኾናል” ሲል ሞገተ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:26 0:00

የኢሰመኮ እና የተመድ የጋራ የሰብአዊ መብት ምርመራ ሪፖርት፥ ለፍትሕ፣ እውነትን ለማውጣት እና ለተጎጂዎች ካሳ “ብቸኛ” መሠረት ኾኖ እንደሚያገለግል፣ ኮሚሽኑ አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት ያቋቋመው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ባለሞያዎች ኮሚሽን፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያወጣውን ሁለተኛ ሪፖርት ትላንት በይፋ ሲያደርግ፣ በኢትዮጵያ፣ የሽግግር ፍትሕን ለመተግበር እየተካሔደ ነው የተባለውን ጥረት አጣጥሏል።

መንግሥት፣ በሽግግር ፍትሕ ሒደቱ ላይ፣ ከባለሞያዎች ኮሚሽኑ ጋራ ንግግር እንደሌለውም ጠቅሷል። በጀኒቫ የቀረበውን የኮሚሽኑን ሪፖርት አስመልክቶ፣ በስፍራው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶር. ዳንኤል በቀለ፣ ለኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሒደት፣ እንደ መነሻ ሊያገለግል የሚችለው፣ የእርሳቸው ተቋም ከተመድ ጋራ ያዘጋጀው የምርመራ ሪፖርት እንደኾነ ሞግተዋል፡፡

የዚኽንም ምክንያት ያስረዱት የኢሰመኮ ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፣ ዓለም አቀፉ የባለሞያዎች ኮሚሽን ሥራውን በርቀት ማከናወኑንና የጣምራ ምርመራው ሪፖርት በኢትዮጵያ መንግሥት ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅሰው አብራርተዋል፡፡

“በኢትዮጵያ፣ የጦር ወንጀሎች እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ አሁንም ቀጥለዋል፣” ያለው ዓለም አቀፉ የባለሞያዎች ኮሚሽን፣ በዐማራ ክልል ያለው ግጭት መባባሱን ጠቅሶ፣ የሥራ ጊዜው እንዲራዘም ጠይቋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG