የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት(IGAD)፣ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የተደረገው ድርድር ያለስምምነት ቢጠናቀቅም፣ ወደፊት ተጨማሪ ንግግሮች ይኖራሉ፤ የሚል ተስፋ እንዳለው አስታውቋል።
በኢጋድ እና በዓለም አቀፍ አጋሮች ድጋፍ፣ በፌዴራሉ መንግሥት እና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚንቀሳቀሰው ዐማፂ ቡድን መካከል፣ በታንዛኒያ - ዳሬ ሰላም ከተማ የተካሔደው ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር ያለውጤት ተጠናቋል።
በሌላ በኩል፣ ግጭት የቀጠለባቸው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ነዋሪዎች፣ ድርድሩ ያለውጤት መጠናቀቁ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፣ ሦስተኛ ዙር ድርድር እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል።