ዋሺንግተን ዲ.ሲ.- አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብዛኛውን የአባይ ወንዝ ግብፅና ሱዳን እንዲጠቀሙ ያደርጋል የተባለ የቅኝ ግዛት ዘመን ውል የሚተካ ውል ዛሬ አፅድቋል።
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ33ተኛው መደበኛ ስብሰባው ከመከረባቸው አምስት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን የአባይ ተፋሰስ የትብብር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ እንዳፀደቀ የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አያና ከበደ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ስምምነቱ አባይን በጋራና በፍትሃዊ መንገድ ለመጠቀም በተፋሰሱ አባላት አገሮች ካሁን ቀደም ኢንቴቤ-ዩጋንዳ ውስጥ የተፈረመ መሆኑ ይታወቃል።
ከኢትዮጵያ በስተቀር አምስቱ አገሮች ማለትም የርዋንዳ፣ የታንዛኒያ፣ የዩጋንዳ፣ የኬንያና የቡሩንዲ ፓርላማዎች ቀደም ብለው ውሉን ያፀደቁት መሆኑን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ተናግረዋል።
የኢንቴቤ ስምምነት እየተባለ የሚጠራው ውል ቅኝ ገዢ በነበረችው ታላቋ ብሪታኒያ በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ1929 ዓ.ም የተረቀቀና በናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ ከተፋሰስ አገሮች ይልቅ ለግብፅ ሙሉ መብት የሚሰጠውን ውል የሚተካ መሆኑ ይታወቃል።
ውሉ ዛሬ በኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ሰሞኑን በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ ከሚካሄደው ውዝግብ ጋር ግንኙነት እንደሌለው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
ይህ ዛሬ የጸደቀው ውል ምንድነው? አቶ አያና ይናገራሉ፡፡
ለተጨማሪና ዝርዝር ትዝታ በላቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት የሕዝብ ግንኙት ባለሙያ አቶ አያና ከበደ ጋር ያካሄደችውን ሙሉ ቃለምልልስ ያድምጡ፡፡