በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቅዱስ ሲኖዶሱ ‘አቡነ መርቆርዮስ ቀደም ሲል በተወሰነላቸው መሠረት መመለስ ይችላሉ’ አለ


መንበረ-ፓትረያርክ
መንበረ-ፓትረያርክ





please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ብፁዕ አቡነ ናትናዔል
ብፁዕ አቡነ ናትናዔል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶች፣ በሰሜን አሜሪካው የሰላምና አንድነት ኰሚቴ አስተናጋጅነት፣ ፫ኛውን እርቀ-ድርድር ባለፈው ረቡዕ ዳላስ፣ ቴክሳስ ውስጥ መጀመራቸው፤ ለዚሁ ውይይት፣ ያዲሳባው ቅዱስ ሲኖዶስ ፬ ልዑካን፣ የስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ፬ ልዑካን እየተሳተፉ መሆናቸው ይታወቃል። ምን ላይ ናቸው? እስካሁን የሰማንው ነገር የለም፣ ደውለን ለማግኘት ያደረግንው ጥረትም አልተሳካም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ማክሰኞ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ከኢትዮጵያው ፕሬዚደንት ግርማ ወልደ-ጊዮርጊስ የተጻፈ «ከሙሉ ክብርዎና ሥልጣንዎ ወደ አገርዎ ገብተው መንበርዎ ላይ እንዲሆኑ» የሚል፣ ፊርማቸውና ቲተራቸው ያረፈበትን፣ በኋላም እራሳቸው ያረጋገጡትን ደብዳቤ፣ በኋላ ደግሞ በራሳቸው አንደበት ተሰርዞ «በማያገባኝ ነበር የገባሁት» ያሉበትን ማሰማታችንና ማስተላለፋችን ይታወሳል።
ፕሬዘዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ
ፕሬዘዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ

«ደብዳቤው ከተሰረዘ የፓትርያርክ መርቆሬዎስ ወደ አገር አገባብ በምን ሁኔታ ይሆናል? ደብዳቤውስ ከተሰረዘ እንደምን ይጻፋል?» ብለን ጥያቄ ለማቅረብ ስንደውል፣ «የፕሬዚደንቱ ልዩ የፖለቲካ አማካሪ ነኝ» ያሉንን አቶ አሰፋ ከሲቶን አገኘን። «እኔ እንዳነጋግራችሁ ነግረውኛል» ስላሉም ጥያቄዎቹን ለርሳቸው አቀረብንና አወያዩን። ይህንንም አሰምተናል።

አቶ አሰፋ፣ «የፓትርያርክ መርቆሬዎስን ጉዳይ ሲኖዶስ እንጂ ፕሬዚደንቱ የሚወስኑት ነገር አይደለም» ስላሉ፣ ለኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ዐቃቤ-መንበረ-ፓትርያርክ ለብፁዕ አቡነ ናትናዔል ደውለን ይህን ነገሩን።

ፕሬዚደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ደብዳቤውን ለፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሲፅፉ ከኰሚቴ ጋር መሆናቸውን፣ ለአንደኛው አባል ለኢንጄነር አራጋውም ጥሩነህ ግልባጭ ስለተደረገላቸው፣ አንዳንድ ነገሮችን ለመጠየቅ ደወልን። ይሁንና አንጂነር «አሁን ትንሽ አሞኛልና ሲሻለኝ» ስላሉ፣ ይህንኑ ለአድማጭ እንደምናሳውቅ ተስማምተን ተለያየን።

የሆነ ሆኖ የሰላሙ ነገር በዚህ ሁኔታ እያለ፣ የዳላሱ ውይይት እንደምን እየተካሄደ ይሆን? ይልቁንም በሰላሙ ውይይት የሚካፈሉት የሁለቱም ሲኖዶሶች ልዑካንስ ምን ይላሉ? ለመሆኑ ዝምታን የመረጡት ስደተኛው ፓትርያርክስ መቼ ይሆን ለተከታዮቻቸው ምዕመናን ያላቸውን እውነት የሚተነፍሱት?

ይህ ጉዳይ፣ ቢፈቅዱ ሁሉንም ወገን ይዘን የምንወያይበት ይሆናል።

ባይፈቅዱ ደግሞ ቤተ-ክርስቲያንን በጉልበቱና በገንዘቡ የሚረዳውን ምዕመን ጋብዘን የምንመለስበት መሆኑ አይቀርም።

ዘገባውን ያዳምጡ

ላሁኑ «ሰላም ያውርድ» እንላለን።
XS
SM
MD
LG