በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ “ድምፃችን ይሰማ” ሰልፍ በአዘጋጆቹ ተሠረዘ


የ “ድምፃችን ይሰማ” ሰልፍ በአዘጋጆቹ ተሠረዘ
የ “ድምፃችን ይሰማ” ሰልፍ በአዘጋጆቹ ተሠረዘplease wait

No media source currently available

0:00 0:07:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ፌደራል ፖሊስ ትናንት ሐሙስ ሐምሌ 25/2005 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “… አክራሪዎች በመስጊዶች ውስጥ የሚያካሂዱትን የጥፋት ድርጊት ለማስቆም …” በሚል “ተገቢውን እርምጃ እና አስፈላጊውን እርምጃ” የሚወስድ መሆኑን በማስታወቅ አስጠንቅቋል፡፡

“የሮመዳን ፆም ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ወቅት ሰላምን ለማወክ እና በየመስጊዶቹ ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ አክራሪዎች ሕገወጥ ቅስቀሣዎችን እያደረጉ ይገኛሉ” ብሎ በ “አክራሪዎቹ” ላይ “እወስዳቸዋለሁ” ላለው “እርምጃ” ኅብረተሰቡ እንዲተባበረው ጠይቋል፡፡

የሠልፉ አዘጋጆች በተለያዩ መንገዶችና በብዝኃሚድያ ባሠራጩት ጥሪ በሮመዳን የመጨረሻ ጁምዓ ዕለት በአዲስ አበባው ፍልውኃ ተውፊቅ መስጂድ እና ከአርባ በላይ ከተሞች ውስጥ ሰዉ የተቃውሞ ድምፁን በሰላማዊ ሁኔታ እንዲያሰማ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG