በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእገታዎች እና ጥቃቶች መባባስ ከየብስ መጓጓዣዎች እየራቁ መኾናቸውን መንገደኞች ገለጹ


በእገታዎች እና ጥቃቶች መባባስ ከየብስ መጓጓዣዎች እየራቁ መኾናቸውን መንገደኞች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚፈጸሙ እገታዎችና ሌሎች ጥቃቶች የፈጠሩት ስጋት፣ ከየብስ ማጓጓዣ አማራጮች እያራቃቸው እንደኾነ የገለጹ መንገደኞች፣ ለተጨማሪ የአየር መጓጓዣ ወጪ እንደዳረጋቸው ተናግረዋል።

ከሐዋሳ አዲስ አበባ የሚመላለሱ መንገደኞች፣ ለወትሮው በመኪና መጓዝ ቀዳሚ ምርጫቸው እንደነበር ገልጸው፣ አልፎ አልፎ በሚሰሙ የጥቃት ዜናዎች ሳቢያ ግን አውሮፕላን ለመጠቀም እንደተገደዱና ይህም ለተጨማሪ ወጪ እየዳረጋቸው እንደኾነ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃነ ዘሩ፣ በአገሪቱ በሕዝብ ማመላለሻዎች የሚጠቀሙ ተጓዦች ቁጥር መቀነስ እየታየበት ነው፤ ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የአገር ውስጥ መንገደኛች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋራ ሲነጻጸር፣ የ34 በመቶ እድገት ማሳየቱን አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG