በዐማራ ክልል በተስፋፋው ግጭት ምክንያት ከወጣው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጋራ በተያያዘ፣ በተለያዩ አምስት ስፍራዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ዜጎች ቁጥር 764 እንደኾነ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ መርማሪ ቦርድ አስታወቀ፡፡
ብዛቱ ወደፊት በተለያዩ ምክንያቶች ሊቀነስ ወይም ሊጨምር እንደሚችልም፣ መርማሪ ቦርዱ አመልክቷል፡፡
የታሳሪዎቹን ቁጥር በአሁኑ ወቅት በትክክል ማወቅ እንዳልቻለ የገለጸው ደግሞ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ነው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።