በኢትዮጵያ ዘንድሮ ያካባቢና የከተማ ምክር ቤቶች ምርጫ በቅርቡ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
ምርጫ ቦርድ እስካለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀርበው የምርጫ ምልክቶቻቸውን ያልወሰዱ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ መሣተፍ አይችሉም ብሏል።
ቅሬታ ያቀረቡ ፓርቲዎች ግን የምርጫ ቦርድ ከምርጫው በፊት የምርጫው ሜዳ እንዲስተካከል ላቀረብናቸው ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ባለመስጠቱ ለመወዳደር እንቸገራለን ብለዋል።
ሰሎሞን ክፍሌ የምርጫ ቦርድ ባለሥልጣንና የተቀዋሚ ፓርቲዎቹን ኮሚቴ ጊዜአዊ ሰብሳቢ አነጋግሯል።
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ