No media source currently available
በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት ኢትዮጵያ ዛሬም ሰላማዊውን መንገድ እንደምትመርጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ይሄንን ለማድረግ ደግሞ የሱዳን ኃይሎች ወደነበሩበት ሥፍራ መመለሳቸው ቀዳሚ ሁኔታ እንደሆነም አሳሰበ።