ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እና ወላጆቻቸው መነሻ ባህላቸውን እንዲያውቁ፣ የአካል እና የመንፈስ ጤናቸውን እንዲጠብቁ ለማስቻል፣ በድምፃዊት እና ተወዛዋዥ ፋንትሽ በቀለ አማካይነት የተመሠረተው መርሐ ግብር፣ ከሰሞኑ አምስተኛ ዓመቱን አክብሯል።
በአሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ ውስጥ በተከናወነው ልዩ ዝግጅት ላይ፣ ሕፃናት እና ወጣቶች፥ ባህላዊ ውዝዋዜ እና የአካል ብቃት ኅብረ ትርኢት አቅርበዋል። የመሰል መርሐ ግብሮች ፋይዳም ተመላክቷል።
ሙሉ ዘገባው ከሥር ተያይዟል።