የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በርበራ ላይ ሊመሠረት ለታለመው የጦር መደብ የሚሆን በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
ኃይሉ ስላለበት ወቅታዊ ቁመናና ስለሚያከናውናቸው ተግባራት አዛዦቹ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ሪፖርት አቅርበዋል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የፈረሙ የመግባቢያ ሰነድ ጉዳይ የሳበው ትኩረትና አነጋጋሪነት እንደቀጠለ ነው።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና መሥሪያ ቤት ከጎበኘ በኋላ በባሕር ኃይል ወቅታዊ አቋም ዙሪያ ከአመራሩና ከአዛዦቹ ጋር ተወያይቷል።
የዚህን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡