በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለደቡብ ኢትዮጵያ ውሳኔ ህዝብ ማስፈፀሚያ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተፈቀደ


ለደቡብ ኢትዮጵያ ውሳኔ ህዝብ ማስፈፀሚያ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተፈቀደ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:30 0:00

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በመጪው ጥር 29 ቀን ለሚያካሒደው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ማስፈፀሚያ ከመንግሥት የ400 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት እንደተፈቀደለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በደቡብ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ህዝበ ውሳኔውን ለማካሔድ የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑንም የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ተናግረዋል፡፡ ቦርዱ ህዝበ ውሳኔውን ለማካሔድ አንድ የማስተባበሪያ ፅ/ቤት እና 24 የማዕከላት ፅ/ቤቶችን ለማደራጀት እየሰራ ቢሆንም ከመንግሥት አካላት በቂ ምላሽ እያገኘን አይደለንም ብለዋል ዋና ሰብሳቢዋ፡፡

XS
SM
MD
LG