1ሺሕ445ኛው የዒድ አል ፈጥር የረመዳን ጾም ፍቺ በዓል፣ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በድምቀት ተከብሯል፡፡
በዓሉ፣ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት መከበር እንዳለበት፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የበዓሉ ታዳሚዎች ገልጸዋል፡፡
የዘንድሮው ዒድ አል ፈጥር፣ በክልሉ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና በኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መካከል ተቋርጦ የቆየው ግንኙነት በዕርቅ ዳግም ከቀጠለ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረ በዓል ነው፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።