በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተፈናቀሉ ሰዎች የእርዳታ ተማጽኖ አቅርበዋል


ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተፈናቀሉ ሰዎች የእርዳታ ተማጽኖ አቅርበዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:56 0:00

በዚህ ዓመት በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሠራዊትና M23 በሚባለው አማፂ ቡድን መካከል የተካሄዱ ግጭቶች ከ160ሺበላይ ማፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር አስታውቋል።

ሬቤካ ኒራኩንዶ የተባለቸው የ20 ዓመት ሴት ባላፈው ሰኔ በኮንጎ ጦርና በአማጽያኑ መካከል በሩትሹሩ ግዛት የተካሄደውን ግጭት በመሸሽ ከባሏና ከአንድ ዓመት ልጇ ጋር ተፈናቅላለች።

ከኒራጎንጎ ግዛት ከመጡ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ጋር ወደ መጠለያ ሠፈርነት በተቀየረ ትምህር ቤት ውስጥ አርፋለች።

ሪቤካ ኒራኩንዶ የተባሉ ተፈናቃይ “እዚህ የደረስነው በእግር ተጉዘን ነው ምክንያቱም ምንም ዓይነት ትራንስፖርት አልነበረንም፤ ምግብ ደግሞ አልነበረንም፤ ምግብ ሳላበስል ለአምስት ቀናት ተጉዣለሁ፤ ልጄ በዚህ የተነሳ ደክሟል፤ አልረዳውም እንጂ ወደ ጤና ተቋም ወስጄው ነበረ።” ብለዋል።

ልጇ በረሃብ ላይ በሽታ ተጨምሮበት የዛሬ ሁለት ሣምንት ሐምሌ 10 ሞተ።

አዳዲስ ተፈናቃዮች አሁንም ካኛሩቺንያ እየገቡ ነው፤ በዚህ የተነሳ ያለችዋም ጥሪት እየተመናመነች ነው።

ቴዎ መስኩራ በካንያሩችኒያ የተፈናቃዮቹ ካምፕ መሪ ነው። “እዚህ ከደረስን አንስቶ ምንም እርዳታ አላገኘንም። እስካሁን በውኃ ጥም፣ በምግብና በመጠለያ እጦት የሞቱ አራት ሰዎችን ቀብሬያለሁ። በጣም እየተሰቃየን ነው።” ብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር (ዩኤንኤችሲአር) ካለፈው መጋቢት ጀምሮ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ሠራዊትና በM23 አማፂያን መካከል የተካሄዱ ግጭቶች ከ160ሺበላይ ሰው ከየቤቱ አፈናቅሎ አብርሯል።

ዩኤን ኤች ሲ አር ግጭቱ ከመቀስቀሱ በፊት ለኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከጠየቀው 225 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ያገኘው አንድ አምስተኛውን ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ካኛሩቺንያ ያለው አንድ አነስተኛ ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል በመሆኑ የህክምና ችግሩም የበረታ ነው።

ማምቦ ከዋያ በኒራጎንጎ ሲቪል ማህበረሰብ አባል ሲሆን፤ “ሆስፒታሉ በፕሬዚዳንቱ አመራር የተሠራው የዛሬ መቶ ዓመት ነበር። ይሁን እንጂ በመሣሪያም ሆነ በሌላ ምንም አቅርቦት የተሟላና የተሻሻለ ነገር የለም። በቅርብ ጊዜ መንግሥት የሰጠው ምንም ነገር የለም። ግጭቱም በጤና አገልግሎት ላይ ችግሮች አሳድሯል።” ብሏል።

በሌላም በኩል በዚህ ሣምንት ውስጥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አሰካባሪ ተዕልኮ ላይ የታየው ተቃውሞ ወደ ሁከት ተለውጦ ቢያንስ 15 ሰው ተገድሏል።

የሰልፈኞቹ ቅሬታ “የሰላም አሰከባሪ ኃይሉ አካባቢያቸውን ማረጋጋትም ሆነው ደኅንነታቸውን መጠበቅ አልቻለም” የሚል ነው።

ለአካባቢው የፀጥታ መደፍረስ የመንግሥታቱ ድርጅት አቃቢያነ ሰላም ተጠያቂ ሆኑም አልሆኑ ጎማ አካባቢ ባሉ ከተሞች ግን ሰላም ብርቅ ነች።

/ዘገባ ከሰሜናዊቱ ጎማ ከተማ በስተምሥራቅ ባለቸው ኒራጎንጎ ከተማ መጠለያ ሠፈሮችን የጎበኘችው ሩት ኦማር ነው//

XS
SM
MD
LG