No media source currently available
በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ተቀስቅሶ በነበረ ግጭት ሰባት ሰዎች እንደተገደሉና ዛሬ ቀብራቸው እንደተፈፀመ ታወቀ፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ከተማውን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ አንፃራዊ ሰላም እንዳገኘችም ተገልጿል፡፡ ፖሊስ የደረሰውን ጉዳት ለይቶ ለማወቅ አንድ ቡድን ማቋቋሙን ተናግሯል፡፡