No media source currently available
የድሬዳዋ ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብ በአማራ ክልል ሞጣ ከተማ የተፈፀመውን የመስጊድ ቃጠሎ በማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል። በከተማዋ ባለፈው አርብ ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ የቁልቢ ገብርዔል ዓመታዊ ንግስ ከተከበረ በኋላ እንዲካሄድ በመወሰኑ ነው ትላንት ሰኞ ዕለት ሰልፉ የተካሄደው። ሰልፉ ያለምንም ችግር በሰላም መጠናቀቁም ተገልጿል።