በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ዳያስፐራ - በዋሽንግተን ዲሲ - ለወጣቶች


ሊያ ከበደ - ዓለምአቀፍ ሱፐር ሞዴል
ሊያ ከበደ - ዓለምአቀፍ ሱፐር ሞዴል



የዓለም ዳያስፐራ ፎረም - 2013
የዓለም ዳያስፐራ ፎረም - 2013

please wait

No media source currently available

0:00 0:33:31 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በዓለም ዙሪያ ከሃገሮቻቸው ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ዕምቅ አቅም ለየወጡባቸው ሃገሮችና ማኅበረሰቦች ጥቅም ሊውል የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ለማበረታታት የታሰበው የዓለም ዳያስፐራ መድረክ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ግንቦት 5 እና 6 / 2005 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡
የዓለም ዳያስፐራ መድረክ - 2013 በዋሽንግተን ዲሲ
የዓለም ዳያስፐራ መድረክ - 2013 በዋሽንግተን ዲሲ
በመድረኩ ላይ በበርካታ የግል የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ የሚሠሩ ስመ ገናና ኢትዮጵያዊንና ኤርትራዊያን የተሣተፉ ሲሆን ከዓለም ዙሪያ የዳያስፐራው አባላት የሆኑ ከአንድ መቶ በላይ ሃገሮች የተገኙበት ነው፡፡

የዛሬ ሦስት ዓመት ተጠንስሶ ለሦስተኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለው ዓለምአቀፍ የዳያስፐራ መድረክ “የሃሣብና የተግባር መገናኛ ሥፍራ” የሚል መርኅ ያለው ነው፡፡

የትውልድ ሃገሩን እየጣለ ወደ ሌሎች ሃገሮች የሚፈልሰው ሰው ቁጥር ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በሦስት እጥፍ የጨመረ ሲሆን ዛሬ በዓለም ዙሪያ ከ215 ሚሊየን በላይ ሰው በውጭ እንደሚኖር በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

ሰዎች ሃገሮቻቸውን እየጣሉ የሚወጡት በኢኮኖሚ ምክንያቶች፣ ደህንነት ፍለጋና በውጭ ከሚኖሩ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል ሲሆን ከሚወጣው ሰው የበዛው ግን ከትውልድ ሃገሩ ጋር ያለው ቁርኝት እንደቀጠለ እንደሚኖር በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

ዶ/ር ራጅ ሻህ - የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ - ዩኤስኤአይዲ ዋና አስተዳዳሪ
ዶ/ር ራጅ ሻህ - የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ - ዩኤስኤአይዲ ዋና አስተዳዳሪ
የዓለም ባንክ ባወጣው መረጃ መሠረት በዓለም ዙሪያ በዳያስፐራ ከሚኖሩ ሰዎች ወደ ትውልዳቸው ወይም ወደ ሌሎች ሃገሮች የተንቀሣቀሰው ገንዘብ በ2011 ዓ.ም 381 ቢሊየን ዶላር መድረሱን እና ይህ ቁጥር በመጭዎቹ ዓመታት ከሰባት እስከ ስምንት ከመቶ በሆነ መጠን እያደገ እንደሚሄድ የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ - ዩኤስኤአይዲ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ራጅ ሻህ በስብሰባው ላይ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በስብሰባው ላይ ንግግር ያደረጉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ራበርት ሃርማትዝ “የዳያስፐራው ማኅበረሰብ አባላት በዓለም ዙሪያ እስከየቤቱ የገባ የአሜሪካ አምባሣደሮች ናቸው” ብለዋል፡፡

ራበርት ሃርማትዝ - የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ራበርት ሃርማትዝ - የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ሚኒስትሩ አክለውም “… የዳያስፐራው አባላት ለዩናይትድ ስቴትስ ቋንቋዎችን፣ ባሕሎችን፣ የሥራ ዕድሎችን፣ በንግድ ሥራ ውስጥ አደጋዎችንና ሥጋቶችን የማሸነፍና የማስወገድ ልምድን፣ የሣይንስና ቴክኖሎጂ ሃሣቦችንና ችሎታን፣ እንዲሁም የበጎ ፍቃደኝነት መንፈስን ይዞ የመጣ ነው፤ ብለዋል፡፡

የቪኦኤ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ኤንሶር ዓለምአቀፏን ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደን በዓለም ዳያስፐራ ፎረም - 2013 ላይ ሲያነጋግሩ
የቪኦኤ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ኤንሶር ዓለምአቀፏን ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደን በዓለም ዳያስፐራ ፎረም - 2013 ላይ ሲያነጋግሩ
በመድረኩ ላይ የዓለም የምግብ ሽልማት አሸናፊው ኢትዮጵያዊ ሣይንቲስት ዶ/ር ገቢሣ ኢጀታ፣ ዓለምአቀፍ ሱፐርሞዴል ሊያ ከበደ፣ ኤርትራዊው የኦሊምፒክ ባለሜዳልያና የኒውዮርክ ማራቶን አሸናፊ መብ ክፍለዝጊ፣ በአሜሪካ የአፍሪካ ሴቶች አውታር መሥራችና ዋና ዳይሬክተር ሰምሃር አርአያ ተገኝተዋል፤ ንግግሮችን አድርገዋል፡፡

የሦስተኛው የዓለም ዳያስፐራ መድረክ ስፖንሰር ከሆኑ ኩባንያዎችና የሚድያ ተቋማት መካከል የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ አንዱ ነው፡፡

ለዝርዝርና ለተጨማሪ መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG