በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲትሮይት ከሠረች


ዲትሮይት - ሚሺጋን

በአንድ ወቅት የአሜሪካ ኢንዱስትሪ ኃያል አቅም ማሳያ ሆና የቆየችው የሰሜን ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትሷ ሚሺጋን ስቴት ትልቋ ከተማ ዲትሮይት መክሠሯን አታወቀች፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በአንድ ወቅት የአሜሪካ ኢንዱስትሪ ኃያል አቅም ማሳያ ሆና የቆየችው የሰሜን ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትሷ ሚሺጋን ስቴት ትልቋ ከተማ ዲትሮይት መክሠሯን አታወቀች፡፡

በከፍተኛ ፍጥነት እየቀነሰ በሄደው የነዋሪዋ ቁጥርና የአቋማቸው አስተማማኝነት ብዙ ጊዜ እየዋዠቀ መምጣት የሕልውናዋን መሠረት ያናጉት ዲትሮይት እንዲህ ዓይነቱን የኪሣራ ዶሴ ስትከፍት በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ውስጥ ግዙፏ ከተማ ሆናለች፡፡

የዛሬ ሃምሣ ዓመት ብዙው ሰው ወደ ባለ መካከለኛ ገቢ ዜጋነት እንዲያድግ ያደረጉት የዲትሮይት የመኪና ፋብሪካዎች ወደ ሁለት ሚሊየን የሚጠጋ ቁጥር ያለውን ሰው በቋሚ ነዋሪነት ስበው እንደነበር ይታወቃል፡፡
ከነዋሪዎቹ መካከል የእነዚያ ፋብሪካዎች የመገጣጠሚያ መሥመሮች ሠራተኞች ሆነው ነበር፡፡

የከተማይቱ የገንዘብና በጀት ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ትናንት - ሐሙስ የከተማይቱን መክሰር በይፋ ያስታወቀውን ዶሴ ሲከፍቱና ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲያስገቡ የነዋሪዎቿ ቁጥር ወደ ሰባት መቶ ሺህ ማሽቆልቆሉን አስታውቀዋል፡፡

ብዙዎቹም ቤቶቿ ያለ ሰው ቀርተዋል፤ ብዙዎች የመኖሪያ መንደሮቿ ባድማ ሆነዋል፡፡

ዴትሮይት ለፌደራል መንግሥቱ ያስገባችው የኪሣራ ማስታወቂያ ከአበዳሪዎቿ ከለላን እንድታገኝ የሚያደርጋት እንደሆነ ታውቋል፡፡
እርምጃቸው ለከተማይቱ አዲስ ጅምር ይሆናል ሲሉ ከንቲባዋ ዴቭ ቢንግ ተናግረዋል፡፡

ዳትሮይት የ300 ሚሊየን ዶላር የበጀት ጉደለት ያለባትና 18 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ የብድር ዕዳ ያለባት ከተማ ነች፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር ዘገባው የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG