በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካማላ ሃሪስ የአውሮፓ ጉዞ፤ ኪየቭ፣ ኔቶና መስኮብ


የካማላ ሃሪስ የአውሮፓ ጉዞ፤ ኪየቭ፣ ኔቶና መስኮብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:08 0:00

በሩሲያና በዩክሬን ጉዳይ ላይ ያተኩራል በተባለ ጉዞ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ ዛሬ ወደ ምዩኒሽ-ጀርመን ሄደዋል።

በሌላ በኩል በሩሲያ ላይ “የቅጣት ውሳኔ ለማሳለፍ” በሚል እየተነጋገረ ያለው የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አንዳች ወጥ ማዕቀፍ ላይ መስማማት የተሳነው መሆኑ ተነግሯል።

ምክትል ፕሬዚዳንት ሃሪስ ወደ ምዩኒሽ የተጓዙት መስኮብ ጦሯን ከዩክሬን ድንበር አካባቢዎች ከማንሳት ይልቅ እንዲያውም እያጠናከረች መሆኗን ሰላሣ አባል አገሮች ያሉት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ትብብር ድርጅት /ኔቶ/ ዋና ፀሃፊ የንስ ሽቶልተንበርግ ለወታደራዊው ህብረት የመከላከያ ሚኒስትሮች በተናገሩ ማግሥት መሆኑ ነው።

ኔቶም ሆነ ሩሲያ ዲፕሎማሲን እንደሚመርጡ ቢነገርም ውጥረቱን ለማርገብም ይሁን ወታደሮቻቸውንና መሣሪያዎቻቸውን ለማራቅ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ያደረጉት እንቅስቃሴ እንደሌለ ሽቶልተንበርግ አመልክተዋል።

የሁሉንም ሥጋቶች ሊያስወግዱ ይችላሉ ያሏቸውን ሃሳቦች ማቅረባቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ ዋሺንግተንም ሆነች የኔቶ አጋሮቿ ለሩሲያ ቁልፍ ጥያቄ የሆነውን የዩክሬንን ከኔቶ ውጭ የመሆን ሃሳብ አልተቀበሉም፤ ወይም ውድቅ አድርገዋል።።

በሌላ በኩል ደግሞ ምናልባት ሩሲያ ወረራ ብትፈፅም የዩክሬን ወገንተኛነታቸውን በአንድ አቋም የሚናገሩት የአሜሪካ እንደራሴዎች በማዕቀቦች አጣጣል ላይ ግን ስምምነት ላይ መድረስ ተስኗቸዋል።

XS
SM
MD
LG