በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልል የጸጥታ ችግር የእናቶች እና ሕፃናት ሞት እንዲጨምር አድርጓል


የአማራ ክልል የጸጥታ ችግር የእናቶች እና ሕፃናት ሞት እንዲጨምር አድርጓል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:08 0:00

: በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ የጸጥታ ችግር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባስከተለው የሕክምና ዕጦት 20 እናቶች እና 74 ጨቅላ ሕፃናት መሞታቸውን፣ እንዲሁም 134 ሞተው የተወለዱ ሕፃናት መመዝገባቸውን፣ የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።

የዞኑ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ጦርነት ወቅት የወደሙት የጤና ተቋማት መልሰው አለመገንባታቸው፣ ከወቅታዊው የጸጥታ ችግር ጋራ ተዳምሮ የሞት ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት ኾኗል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የዞኑ ነዋሪዎችም፣ በቂ የሕክምና አገልግሎት ባለመኖሩ እየተሠቃዩ እንደኾነ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG