ቻይናን አስመልክቶ ለረጅም ጊዜ ሲንተከተክ የቆየ የጥላቻ ስሜት በቤጂንግ በመካሄድ ላይ ባለው የክረምት ኦሎምፒክ በያዝነው ሳምንት በኦሎምፒክ አደባባይ የተቀሰቀሱ ሁለት ውዝግቦችን ተከትሎ በፍጥነት መቀጣጠል ይዟል።
ውዝግቡ የተቀሰቀሰው “ሀንቡክ” በመባል የሚታወቀውን ሮዝ ቀለም ያለው የኮርያውያን ባሕላዊ ቀሚስ የለበሰች አንዲት ሴት በኦሎምፒክ
መክፈቻው ሥነ-ስርዓት ላይ የቻይናን ባንዲራ እያውለበለበች በታየችበት ወቅት ነበር።
ቤጂንግ ከፍተኛ ዝና እና ተወዳጅነት ባላቸው የደቡብ ኮሪያ ባህል ገፅታዎች ላይ በይገባኛል ስሜት ታንጽባርቃለች በሚል በደቡብ ኮሪያውያን ዘንድ ከምትወነጀልበት ድርጊት እንደ አንዱ አድርገው የወሰዱ ደቡብ ኮሪያውያን ያደረባቸውን ከባድ ቁጣ ይዘው አደባባይ ወጥተዋል።
ውድድሩ ከተጀመረ በኋላም ነገሮች ይበልጥ እየተባባሱ ሄዱ። ባለፈው ሰኞ በተካሄደ አንድ ውድድር፣ የአጭር ርቀት ፈጣን የበረዶ ሸርተቴ ጫወታ በወዳደር ላይ የነበሩ ሁለት ደቡብ ኮሪያያውያን ተወዳዳሪዎች የጫወታውን ህግ የተላለፈ እንቅስቃሴ አድርጋችኋችል በሚል ከውድድሩ ውጪ ተደረጉ። ይህም ለሁለት ቻይናውያን ተፎካካሪዎቸው ወደሚቀጥለው ውድድር እንዲያልፉ በር በመክፈቱና በመጨረሻም የወርቅ እና የብር ሜዳሊያዎች አሸናፊ ለመሆን በመብቃታቸው ነው።
የደቡብ ኮሪያ መገናኛ ብዙኃን የቤጂንግ 2022 ኦሎምፒክ ውድድር ዳኞች “ለቻይና አድልተዋል” በሚል የተሰሙ ቅሬታዎችን አስተጋብተዋል።
"በቃ አስተናጋጇ ሃገር ቻይና ሁሉንም ሜዳሊያዎች ትወስድ” ሲል ጻፈ ሶል ሲንሙን የተባለ የደቡብ ኮሪያ ጋዜጣ በምጸት። ይህንኑ አስተያየት ያዘለ መልዕክቱን 11 ጊዜ በመደጋገም አስነብቧል። ኤስቢኤስ በመባል የሚታወቀው አንድ ታዋቂ የደቡብ ኮሪያ የቴሌቭዥን ጣቢያ በበኩሉ "ቻይና በውድድሮቹ ያጭበረበረችባቸው አስር መጥፎ አጋጣሚዎች”
በሚል የተቀናበረ ካሁን ቀደም ቻይናውያን አትሌቶች የነበሩችባቸውን ውድድሮች ያካተተ ወንጃይ ዝግጅት አሰራጭቷል።
ይህ ፀረ-ቻይና ግርግር የተሰማው ጥብቅ ፉክክር እየታየበት ያለው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ሳምንታት ሲቀረው ነው። ሁለቱም ዋና ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች “በሰኞው ውድድር ትክክለኞቹ አሸናፊዎች ደቡብ ኮሪያውያኑ ተፎካካሪዎች ነበሩ። ባሕላዊውን ልብስ ያሳየችበትም አድራጎት ቻይና የደቡብ ኮርያን ባህል አስመልክቶ የተሳተፈችበት የቅርብ ጊዜ አሉታዊ ድርጊቷ ማሳያ ነው” ሲሉ የየበኩላቸውን ግምገማ ሰንዝረዋል።