No media source currently available
የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት በሰሜን ምሥራቅ ክፍለ ሀገር ቦረኖ (Borno) ካምፕ ውስጥ በቦኮ ሐራም ነውጠኞች ከታገቱ ሰዎች መካከል 61ዱን አስለቀቀ። በዘመቻው ወቅት ወታደሮቹ አራት የነውጠኛውን ቡድን ታጣቂዎች መግደላቸውንና አንድ መማረካቸውን የጦር ሠራዊቱ ቃል አቀባይ ገልጸዋል። ወረራው መቼ እንደተካሄደ ግን አላብራሩም።