በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሊንከን ጉብኝት አንድምታዎች


የብሊንከን ጉብኝት አንድምታዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:55 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ሁለት የአፍሪካ አገራትን ለመጎብኘት ከትናንት በስቲያ ወደ አፍሪካ አቅንተዋል።

በኢትዮጵያ ቆይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ከከፍተኛ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል።

እንዲሁም በትናንትናው ዕለት ባለፈው ጥቅምት የሰላም ስምምነቱን ከፈረሙት የኢትዮጵያ መንግስት ብሔራዊ የጸጥታ አማካሪ ሬድዋን ሁሴን እና ከህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ጋር የሥምምነቱ አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ መወያየታቸው ታውቋል።

ብሊንከን ከኢትዮጵያ ባለሥልታናት ጋር ባደረጉት ውይይት እንዲሁም በማጠቃለያ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያና አሜሪካ ግኑኝነት ወደ ነበረበት መልካም ሁኔታ ከመመለሱ በፊት መንግሥት ከህወሓት ጋር የደረሰውን የሰላም ሥምምነት በመተግበር ረገድ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያሳይ አሳስበዋል።

በየመድረኩ ከተገለጸው በተጨማሪ፣ ለመሆኑ የብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝት ሌሎች አንድምታዎች ይኖሩት እንደሁ ቪኦኤ ሦስት ተንታኞችን አነጋግሯል።

[ሙሉውን ዝግጅት ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG