በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል ግጭት በተባባሰው የግብርና ምርቶች የዋጋ ንረት እንደተማረሩ ነዋሪዎች ገለጹ


 በዐማራ ክልል ግጭት በተባባሰው የግብርና ምርቶች የዋጋ ንረት እንደተማረሩ ነዋሪዎች ገለጹ
please wait
  • Auto
  • 240p
  • 360p
  • 480p
  • 720p

No media source currently available

0:00 6:38 0:00
  • Auto
  • 240p
  • 360p
  • 480p
  • 720p

በዐማራ ክልል፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በፋኖ ቡድን ታጣቂዎች መካከል ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለው ግጭት፣ ለመሠረታዊ የግብርና ፍጆታዎች አቅርቦት ዕንቅፋት እንደኾነባቸውና ለከፍተኛ የዋጋ ንረትም እንደዳረጋቸው፣ አንዳንድ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ፣ ዛሬ ረቡዕ ያነጋገራቸው የልዩ ልዩ ከተሞች ነዋሪዎች፣ ግጭቱ የገበያ ተደራሽነትን በማስተጓጎሉ ምክንያት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ በተለይ እንደ ጤፍ፣ ሽንኩርት እና መሰል መሠረታዊ የግብርና ፍጆታዎች ላይ የዋጋ ንረት እንዳስከተለ አመልክተዋል፡፡

ሸማቾቹ አክለውም፣ ገበያውን መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እንዲቆጣጠረው ጠይቀዋል፡፡

ያነጋገርናቸው አንድ የጤፍ ነጋዴ ደግሞ፣ በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ሳቢያ፣ አርሶ አደሩ ምርቶችን ለገበያ እያወጣ ባለመኾኑ፣ የአቅርቦት እጥረቱ እንዳጋጠመ አስረድተዋል፡፡

የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ምክትል ቢሮ ሓላፊ አቶ ወንደሰን ለገሰ፣ በመሠረታዊ የግብርና ፍጆታዎች ላይ፣ ሰሞኑን ከፍተኛ ጭማሪ እንደታየ አምነው፣ ለዚኽም፣ ከክልሉ የጸጥታ ችግር ጋራ በተያያዘ ተከፍቷል ያሉት ሐሰተኛ መረጃም አስተዋፅኦ ማድረጉን አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG