በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለቀናት በቀጠለው የፈረስ ቤት ግጭት ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት እንደደረሰ ተገለጸ


ለቀናት በቀጠለው የፈረስ ቤት ግጭት ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት እንደደረሰ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:17 0:00

በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ የፈረስ ቤት ከተማ አካባቢ፣ ላለፉት ተከታታይ ሦስት ቀናት በዘለቀው ውጊያ፣ ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት እንደደረሰ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

አስተያየት ሰጭዎቹ፣ እስከ ዛሬ በዘለቀው የመከላከያ ኀይሉ እና የፋኖ ታጣቂዎች ውጊያ፣ በሴቶች እና ሕፃናት ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል፡፡ “በከባድ መሣሪያ ተመታለች፤” ያሏት አንዲት የሁለት ዓመት ሕፃን ደግሞ፣ ከወደመ ቤት ፍርስራሽ ውስጥ በሕይወት እንደተገኘች ገልጸዋል፡፡

በተኩስ ልውውጡ ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉት ንጹሐን ሰዎች እንደኾኑ ያስታወቁት አስተያየት ሰጭዎቹ፣ እውነተኛ የሰላም ጥሪ እና የሰላም ድርድር እንዲኖር ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG