በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል ኹሉም ዩኒቨርሲቲዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ ፎረሙ ገለጸ


በዐማራ ክልል ኹሉም ዩኒቨርሲቲዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ ፎረሙ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:14 0:00

በዐማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ምክንያት፣ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መደበኛ ሥራቸው በቅርቡ እንደማይመለሱ፣ የክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም አስታወቀ፡፡

የፎረሙ ዋና ጸሐፊ ዶር. አስማረ ደጀን፣ ዛሬ ዐርብ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ በክልሉ የሚገኙ ዐሥሩም ዩኒቨርሲቲዎች፣ የክልሉ ጸጥታዊ ኹኔታ እስኪሻሻል ድረስ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ፣ የጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱ ገልጸዋል፡፡

ተለዋዋጭነት ባለው የክልሉ ጸጥታ ምክንያት መንገድ መዘጋቱ፣ ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ግጭት ቢነሣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ሓላፊነት መውሰድ ስለማይችሉ፣ እንዲሁም ከምግብ ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲዎች ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ያቀርቡ የነበሩ አካላት፣ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ማስታወቃቸው፣ ለፎረሙ ውሳኔ መሠረት እንደኾኑ ጸሐፊው አስረድተዋል፡፡

ይኹንና ያነጋገርናቸው ተማሪዎች፣ በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲዎቹ ቢጠሯቸው እንደሚገቡ ገልጸዋል፡፡ የተማሪዎቹ ወላጆች በአንጻሩ፣ የፎረሙን ውሳኔ እንደሚቀበሉት ተናግረዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG