በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ እያሽቆለቆለ የመጣው የልጆች የማንበብ ክህሎት


በደቡብ አፍሪካ እያሽቆለቆለ የመጣው የልጆች የማንበብ ክህሎት
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:56 0:00

በደቡብ አፍሪካ የወጣ አንድ ሪፖርት እንዳመለከተው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወዲህ የልጆች መሠረታዊ የንበብ ክህሎት እጅግ ቀንሷል።

መንግሥት ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚጥር ቢገልጽም፣ በደቡ አፍሪካ ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት የሁለትኛ ክፍል ሕጻናት ፊደላትን ማንበብ እንደማይችሉ ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። አራተኛ ክፍል ከደረሱት አብዛኞቹ ደግሞ፣ መሠረታዊ ንባብ እያዳገታቸው መሆኑን ሪፖርቱ ጠቁሟል። ይህን ለማሻሻልም አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።

2030 የንባብ ቡድን የተሰኘው ስብስብ አባል በሆኑ ግለሠብ የወጣው ሪፖርት እንደጠቆመው አራተኛ ክፍል ደርሰው መሠረታዊ የንባብ ክህሎት የሚያጥራቸው ልጆች ቁጥር ከሰባት ዓመት በፊት ከነበረው 78 በመቶ ወደ 82 በመቶ አድጓል።

ይህንን ለመቀልበስ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ከሚያውሉት ሰዓት 25 በመቶውን ለንባብ በማዋል ላይ ናቸው።

“ከመንግሥት፣ ከግል እንዲሁም ከሞዴል-ሲ ትምህርት ቤቶች የመጡ ተማሪዎችን ተቀብለናል። ሁሉም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ማንበበ አለመቻላቸው ነው። አንድ ቀላል ቃል እንኳ ማንበብ አይችሉም ነበር። ስለዚህ ወደ ኋላ ተመልሰን ሁለተኛ፣ ስድስተኛ አንዳንዴም ስምንተኛ ክፍሎችን ቃላትን

ማንበብ ማስተማር ነበረብን። ይህ ውስብስብ ጉዳይ ነበር ምክንያቱም ስምንተኛ ክፍል የደረሱት “ሃሪ ፖተር” የተሰኘውን መጽሐፍ ካለችግር ማንበብ መቻል ነበረባቸው” ሲሉ ዋሂዳ ቶልበርት ምባታ ክጎሎሎ አከደሚ የተሰኘው ት/ቤት ርዕሰ-መምህር ተማግረዋል።

የጀማሪ ተማሪዎች የትምህርት ሃላፊ የሆኑት ነሊ ምሎንጎ የወላጆች እገዛ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራሉ።

“ወላጆቹ ልጆቻቸውን ለመርዳት እንዲችሉ አንዳንድ ዘዴዎችን ማወቅ ከፈለጉ ወደ ት/ቤቱ መጥተው ከአስተመሪዎቹ ጋር ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ። ይህን ድጋፍ ነው ከት/ቤቱ የሚያገኙት” ብለዋል ነሊ ምሎንጎ።

ኒክ ስፖል በስተለንባሽ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰርና የጥናት ሪፖርቱ አዘጋጅ ናቸው። የደቡብ አፍሪካው መንግስት ዕቅድና ፕላን እንደሚያስፈልገው ይናገራሉ።

“በአሁኑ ወቅት ንባብን በተመለከተ አገራዊ የሆነ ዕቅድ የለም። በጀትም የለም። ዕቅድም ሆነ በጀት ከሌለህ፣ ምንም ዓይነት ለውጥ ማየት አትችልም። በደቡብ አፍሪካ ይለው ትልቁ ችግር የንባብ ችግሩን ለመፍታት የፖለቲካ ቁርጠኝነቱ የለም” ሲሉ ተናግረዋል ስፖል።

በአገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር የሚገኙ ባለሥልጣናት ችግሩን አምነው፣ የትምህርት ቤቶች ተሳትፎና ከክፍል ክፍል የመዘዋወር ሁኔታው ባለፉት 20 ዓመታት እንደተሻሻለ ይናገራሉ።

የመሠረታዊ ትምህርት ክፍል ሃላፊ ስቲፈን ቴለር ችግሩ በደቡብ አፍሪካ ብቻ የተወሰነ አይደለም ይላሉ።

“’የደቡባዊና ምሥራቅ አፍሪካ የትምህርት ጥራት ቁጥጥር’ የተሰኘው ስብስብ ውስጥ ተሳታፊ ነን። በቀጠናው የሚገኙ 14 አገሮች ውስጥ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ በማተኮር በንባብና ሂሳብ ዘርፍ የተደረገ ዓለም አቀፋዊ ጥናት ነው። የንባብ ችሎታ መዳከም በደቡብ አፍሪካ ብቻ የሚታይ ችግር አይደለም። እንደውም በቀጠናው ከአማካዩ በትንሹ ከፍ ያልን ነን” ሲሉ ይሟገታሉ ቴለር።

የትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናቱ እንደሚሉት፣ በርከት ያሉ ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በመመረቅ ላይ በመሆናቸው የአገሪቱ የትምህርት ሁኔታ የብዛት ጭማሪ በማሳየት ላይ ነው።

XS
SM
MD
LG