በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ“ሲድ ኢትዮጵያ”- የዘንድሮ ተሸላሚ ብርቱ ኢትዮጵያውያን


የ“ሲድ ኢትዮጵያ”- የዘንድሮ ተሸላሚ ብርቱ ኢትዮጵያውያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:08 0:00

“ሲድ ኢትዮጵያ”፥ ለሦስት ዐሥርት ዓመታት የዘለቀ አንጋፋ የኢትዮጵያውያን ድርጅት ነው። መልካም የሠሩ ብርቱ እና ጎበዝ ኢትዮጵያውያንን ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ አክብሮት እና ምስጋና ለመቸር የተቋቋመ፣ ለማኅበረሰብ ልዕልና የቆመ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ፣ በዓለም ዙሪያ ለሚኖሩ ውጤታማ ኢትዮጵያውያን በሚሰጠው ዕውቅና፣ ወጣት እና አዳጊ ተስፈኞች እንዲሁም የነገ ባለ አደራዎች ከቀደመው ትውልድ አርኣያ ይነሱበታል፡፡

በትምህርታቸው እጅግ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡትን መርጦ በመሸለም ከማበረታታት ባሻገር፣ ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ለበለጠ ስኬት ለማነቃቃት ይችሉ ዘንድ ዕድል መፍጠር ዓይነተኛ ዓላማዎቹ ናቸው - ለዩናይትድ ስቴትሱ የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት።

የዘንድሮውን ሥነ ሥርዐት የተከታተለው አሉላ ከበደ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG