በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእናቶችና ጨቅላ ህፃናትን ሞት


የእናቶችና ጨቅላ ህፃናትን ሞት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:34 0:00

በኢትዮጵያ በተለይ በገጠርና ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ነፍሰጡር እናቶች ተገቢውን ሕክምና ባለማግኘታቸው ምክኒያት እናቶችና ጨቅላ ሕፃናት እንደሚሞቱ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ።

በምስራቅ ወለጋ ዴዴሳ ቀበሌ ነዋሪዋ ወ/ሮ ሌሊሴ ጃዋር ምስራቅ ከሦስት ቀናት በፊት ለወሊድ ሆስፒታል ቢገቡም ልጃቸውን ግን መታቀፍ እንዳልቻሉ ይናገራሉ።

ግጭት ተከስቶበት በነበረው ራያ ቆቦ ከተማ ነዋሪ እንደሆኑ የሚናገሩት ወ/ሮ ጎዳዳ ሞላ በበኩላቸው በአካባቢው በነበረው ጦርነት ይበልጥ ተጎጂ የነበሩት እናቶችና ህፃናት እንደነበሩ ይናገራሉ።

በአምቦአጠቃላይ ሆስፒታል የፅንስና ማኅፀን ስፔሻሊስት ዶ/ር ኃይሌገመቹ በበኩላቸው ነፍሰ ጡር እናቶችተገቢውን ክትትል የማያገኙ በመሆኑ ለጉዳት እንደሚዳረጉ ገልፀዋል።

በሌላበኩል በኢትዮጵያ በዓመት 14 ሺህ የሚሆኑ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ጤና ሚኒስቴርገጿል። ከ87 ሺህ በላይጨቅላ ህፃናትም በወሊድ ላይ በሚከሰት የጤና እክልህይወታቸው እንደሚያልፍ የጤና አስታውቋል።

በጤና ሚኒስቴር የእናቶች እና ህፃናት ጤና ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ እናቶች እና ጨቅላ ህፃናትን ለመታደግ ሚኒስተሩ በተቀናጀ ሁኔታ ሥራ ጀምሯል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG