ባለፉት ዓመታት ደቡብ አፍሪካ፣ ምጣኔ ሀብቷን በአገባቡ ለማንቀሳቀስ የሚያስችል በቂ የኤሌክትሪክ ኀይል ለማምረት አልቻለችም፡፡
በአፍሪካ አህጉር፣ የበለጸገ ኢኮኖሚ እንዳላት የሚነገርላት ደቡብ አፍሪካ፣ በፈረቃ እየተገበረች በምትገኘው የኀይል ሥርጭት፣ በቀን ከስምንት እስከ 10 ሰዓታት መብራት ለማስተጓጎል ተገዳለች፡፡ ይህም፣ በታላላቅም ኾነ በታናናሽ የንግድ እና የምርት ሥራዎች ላይ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡
በአገሪቱ ሰሜን ምዕራብ አውራጃ፣ በዶሮ ርባታ ላይ የተሠማሩት ኽርማን ዱ ፕሪዝ፣ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ ምክንያት 40 ሺሕ የሚኾኑ ዶሮዎቻቸው ታፍነው ሞተዋል፡፡ ዶሮዎቹ የሚራቡበትን የአየር ኹኔታ ለመቆጣጠር፣ የማያቋርጥ የኤሌክትሪክ ኀይል ያስፈልጋል፡፡ በመኾኑም፣ ሦስት ጄኔሬተሮችን ለማቆም ተገደዋል፡፡
“በዶሮ ማርቢያው ውስጥ ያለው የኀይል መቆጣጠሪያ ጠፍቷል፡፡ መቆጣጠሪያው፣ የዚኽ ቤት መዘውር ነው፤ ለማለት ይቻላል፡፡ ኹሉንም ነገር ነው የሚቆጣጠረው፡፡ ምግብ የሚያቀርበው፣ የቤቱን ሙቀት እና ርጥበት የሚመጥነው እርሱ ነው፤” ሲሉ ተናግረዋል፣ ዶሮ አርቢው ዱ ፕሪዝ፡፡
ዱ ፕሪዝ እንደሚሉት፣ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት እና የግብርናው ዘርፍ ባለሀብቶች ተቀራርበው በመነጋገር፣ የኀይል መቆራረጥ በገበሬዎች ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ የሚቀንስበትን መላ መሻት አለባቸው፡፡ በዚኽም፣ የምግብ ዋጋ እንዲቀንስ ማድረግ ይቻላል፤ ብለዋል፡፡
ሲሉ የኀይል አቅርቦትን ኹኔታ የሚከታተሉት አዲል ቻበለንግ ይናገራሉ - ኹኔታዎች እንደሚሻሻሉ ተስፋ እንደነበራቸው ገልፀው፤ “ትልቅ ኪሳራ የደረሰባቸው ነዋሪዎች፣ በመንግሥት ላይ ቅሬታቸውን ማሰማት ይገባቸዋል።” በማለት አሳስበዋል።