በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል ሻባብ ሞቅዲሾ አካባቢ ባካሄደው ጥቃት ዘጠኝ ሲቪሎች ተገደሉ


የአል-ሻባብ ነውጠኞች ዛሬ ሰኞ ሞቅዲሾ አካባቢ ባካሄዱት ጥቃት ዘጠኝ ሲቪሎችን እንደገደሉ፣ የሶማልያ ባለሥልጣናት ገለፁ።

የአል-ሻባብ ነውጠኞች ዛሬ ሰኞ ሞቅዲሾ አካባቢ ባካሄዱት ጥቃት ዘጠኝ ሲቪሎችን እንደገደሉ፣ የሶማልያ ባለሥልጣናት ገለፁ።

ነውጠኞቹ ጥቃቱን ያካሄዱት በታችኛው ሸበሌ ክልል ላፎሌ ውስጥ መንገድ በማፅዳት ላይ በነበሩ 11 ሲቪሎች ላይ መሆኑን ባለሥልጣናት ጨምረው ገልፀዋል።

ላፎሌ፣ ከሞቅዲሾ በስተምዕራብ 20ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች።

የክልሉ ገዢ ሞሓመድ ኢብራሂም ባሬ ለአሜሪካ ድምፅ ሶማል አገልግሎት በሰጡት ቃል፣ ስድስት ወንዶችና ሦስትሴቶች በነውጠኞቹ ሲገደሉ ሌሎች ሁለት መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይል በታች ሸበሌ ክልል አል-ሻባብ ላይ አራትአዳዲስ የአየር ጥቃቶችን ማካሄዱ ተገለፀ።

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጦር አዛዥ እንደገለፁት፣ ሁለት የነውጠኛው ቡድን ተዋጊዎች የተገደሉበት የጦር ኃይሉ የአየር ጥቃት ያነጣጠረው፣ የአል-ሻባብ ተቋማት በሚያገኛቸው ሥፍራዎች ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG