በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካ ከዓለም ተፈናቃይ ሕዝቦች ግማሹን አስጠልላለች


አፍሪካ ከዓለም ተፈናቃይ ሕዝቦች ግማሹን አስጠልላለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:30 0:00

በግጭት ምክንያት በዓለም ዙሪያ 75ነጥብ9 ሚሊዮን ሰዎች፣ በሀገር ውስጥ መፈናቀላቸውንና ከነዚህ ውስጥ ግማሽ የሚኾኑቱ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት እንደሚገኙ፣ በቅርቡ ይፋ የተደረገ ሪፖርት አስታውቋል።

“የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል” የተሰኘው ተቋም ባወጣው ሪፖርት፣ እ.አ.አ በ2023 ብቻ በቀጣናው 34ነጥብ8 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውን አውስቷል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ጋራ ሲነጻጸር ብልጫ ማሳየቱን ገልጾ፣ በተለይ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በምትገኘው ሱዳን የተፈናቃዮች ቁጥር በከፍተኛ ኹኔታ መጨመሩን አመልክቷል።

በዚህ ጉዳይ ላይ መሐመድ ዩሱፍ ያደረሰንን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።

XS
SM
MD
LG