በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደንጌ ትኩሳት በአፋር ክልል ሰባት ወረዳዎች እንደተከሠተ ተገለጸ


የደንጌ ትኩሳት በአፋር ክልል ሰባት ወረዳዎች እንደተከሠተ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:50 0:00

ከወባ በሽታ ጋራ ተመሳሳይነት እንዳለው የሚነገርለት የደንጌ ትኩሳት፣ በአፋር ክልል በሁለት ዞኖች ባሉ ሰባት ወረዳዎች ውስጥ እንደተከሠተ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡

ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ፣ በበሽታው፥ ከ4ሺሕ700 በላይ ሰዎች እንደተያዙ ቢሮው አስታውቋል፡፡

የሎጊያ ከተማ ነዋሪው ታምራት ሙላት እና ባለቤታቸው፣ ከወባ ጋራ ተመሳሳይነት አለው በሚባለው የደንጌ ትኩሳት በመታመማቸው፣ ሕክምና ወስደው ከአገገሙ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት አልፏቸዋል፡፡

የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ሓላፊ የሲን ሐቢብ እንዳስታወቁት፣ በክልሉ ዞን አንድ አውሲረሱ በሚገኙት ሰመራ፣ ሎጊያ፣ ሚሌ፣ ጭፍራ እና ዱብቲ፣ እንዲሁም በዞን ሦስት ገቢረሱ በሚገኘው ገለአሉ አካባቢ

የደንጌ ትኩሳት ተከሥቷል፡፡ ሕመሙ ከወባ ጋራ ተመሳሳይ ቢኾንም፣ የበሽታው አማጭ የኾነችው ትንኝ፣ የተለየ ባሕርይ እንዳላት፣ ቢሮ ሓላፊው አመልክተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG