በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሄፐታይተስ ቢ”ን የመከላከል ጥረት


ሄፐታይተስ ቢ”ን የመከላከል ጥረት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:06 0:00

ሄፐታይተስ፣ በተላላፊ ቫይረሶች እና ተላላፊ ባልኾኑ ቫይረሶች(HBV) አማጭነት የሚከሠት የጉበት ብግነት ወይም መቆጣት ሕመም ነው።

አብዛኛውን ጊዜ የሕክምና ባለሞያዎች ይህን በሽታ፣ “ድምፅ አልባው በካይ” በሚል ይጠሩታል።

ሄፐታይተስ፣ በዓለም ላይ በየቀኑ 3ሺሕ500 ሰዎችን ለኅልፈት እንደሚዳርግ፣ በቅርቡ ፖርቱጋል ውስጥ በበሽታው ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተካሔደበት ወቅት፣ የዓለም የጤና ድርጅት ይፋ አድርጓል።

በገዳይነቱ ከተላላፊ በሽታዎች በሁለተኛ ደረጃ በሚጠቀሰው “ሂፐታይተስ” ሳቢያ የሚሞተው ሰው ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ ያስጠነቀቀው ድርጅቱ፣ በሽታውን ለመዋጋትም ፈጣን ርምጃ መወሰድ እንዳለበት እያሳሰበ ይገኛል።

ይህንኑ የጉበት ብግነት ወይም መቆጣት በሽታ ዓይነት፣ ምንነት፣ የሚያስትለውን ጉዳት፣ ምርመራውንና ሕክምናውን በተመለከተ ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል፣ የአንጀት እና የጉበት ስፔሻሊስት ዶር. ዮሐንስ ብርሃኑ ማብራሪያ ሰጥተውናል።

XS
SM
MD
LG