በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአበርገሌ እና የጻግብጅ ተፈናቃዮች እየተመለሱ ቢኾንም መሰናክል አላጣቸውም - ዞኑ


የአበርገሌ እና የጻግብጅ ተፈናቃዮች እየተመለሱ ቢኾንም መሰናክል አላጣቸውም - ዞኑ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:46 0:00

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት፣ ከዐማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አበርገሌ እና ጻግብጅ ወረዳዎች ተፈናቅለው፣ በሰቆጣ እና አካባቢው ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እየተመለሱ መኾኑን ዞኑ አስታወቀ።

ተፈናቃዮቹን ወደ ቀዬአቸው የመመለሱ ሥራ እየተከናወነ ቢኾንም፣ አሁንም ድረስ በህወሓት እና ራሱን “የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ” ሲል በሚጠራው ታጣቂ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ቀበሌዎች መኖራቸውን፤ የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ አመልክቷል፡፡

በርካታ ተፈናቃዮች፣ በአበርገሌ ወረዳ ከተማ ኒሯቅ እና በጻግብጅ ወረዳ ከተማ ጻታ አካባቢ፣ በት/ቤቶች ውስጥ ተጠልለው ለመቆየት መገደዳቸውን መምሪያው አስታውቋል፡፡ ራሱን “የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ” የሚለው ታጣቂ ኃይል የውጭ ግንኙነት ሓላፊ ባዬ በሬ ግን፣ ታጣቂዎቻቸው ተፈናቃዮችን ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ላይ ምንም ዓይነት ዕንቅፋት አለመፍጠራቸውን በመግለጽ አስተባብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG