በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሊበንና ባሌ ዞኖች ውስጥ ጥቃቶች ሰውን እያፈናቀሉ ነው


ሊበንና ባሌ ዞኖች ውስጥ ጥቃቶች ሰውን እያፈናቀሉ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:17 0:00

ኦሮምያና ሶማሌ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው ሊበንና ባሌ ዞኖች ውስጥ የተፈፀሙ ጥቃቶችን እየሸሹ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ።

ከሶማሌ ክልል የሚነሱ ታጣቂዎች በሚሠነዝሩባቸው ጥቃት የተነሳ የተፈናቀሉ ናቸው የተባሉና ባሌ የተጠለሉት ብዛት 14 ሺህ መድረሱን የዞኑ አደጋ መከላከል ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ከበደ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል ጥቃቱ ከሶማሌ ክልል ይነሳል መባሉን እንደማይቀበሉ ለቪኦኤ የተናገሩት የዞኑ ፀጥታ ኃላፊ አቶ መሐመድ አብዲ በክልላቸው ሊበን ዞን ጉራ ዳሞሌ ወረዳ ውስጥ ላለፉት 5 ወራት ጥቃት ሲፈፀም መቆየቱንና በዚህም 18 ሰዎች መገደላቸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ እንስሣት መዘረፋቸውን ገልፀዋል።

ተፈናቅለው ወደ አጎራባቾቹ የኦሮምያ ወረዳዎች የሄዱ መኖራቸውን የጠቆሙት አቶ መሃመድ አብዲ “ሁኔታው የተፈጠረው በሶማሌ ክልል ወረዳ ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ ኃይሎች አዋሳኝ የኦሮምያ ቀበሌዎችን መውጫ መግቢያ መንገድ ጭምር በመዝጋታቸው ነው” ብለዋል።

በሁለቱም በኩል ላለመረጋጋቱ ከሌላኛው ክልል የሚነሳ ታጣቂን ሲወነጅሉ እንደምክንያት የሚያቀርቡትም “የመስፋፋት ፍላጎት መኖሩን” ነው።

ከቀናት በፊት በሁለቱ ክልሎች ምክትል ርዕሳነ መስተዳድር የተመራ የምክክር መድረክ መዘጋጀቱ የተነገረ ሲሆን ያስገኘው ውጤት እንዳለ ለጊዜው አልታወቀም።

XS
SM
MD
LG