No media source currently available
በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ወደ አገር መመለሳቸው ለዘንድሮው የገና በዓል የተለየ ድምቀት እንደሰጠው ሃሳቦቻቸውን ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ያካፈሉ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል። በብዙ ቁጥር ወደ አገር መግባታቸውን "ኢትዮጵያን በተመለከተ እየተሠራጨ ያለውን የተዛባ መረጃ ማጋለጥ የቻልንበትና ያሸነፍንበት ነው" ያሉም አሉ።