በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት ቢመለስም “የሚያስጠቅም አለመኾኑን” ነዋሪዎች ተናገሩ


በዐማራ ክልል የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት ቢመለስም “የሚያስጠቅም አለመኾኑን” ነዋሪዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00

የዐማራ ክልል ርእሰ መዲና በኾነችው ባሕር ዳር፣ ለወራት የተቋረጠው የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት እና በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የተጣለው እገዳ፣ በከተማዋ ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና ከመፍጠሩም ባለፈ፣ የነዋሪዎችን መረጃ የማግኘት መብት መገደቡን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች፣ እንደ አማራጭ፣ ባለገመድ የኢንተርኔት አገልግሎት በቤታቸው ቢያስገቡም፣ በተለይ በዚኽ ሳምንት ፍጥነቱ እጅግ ዝቅተኛ በመኾኑ፣ ሥራቸውን ማከናወን እንዳልቻሉ አመልክተዋል፡፡

በክልሉ ተቋርጦ የነበረው የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት፣ ትላንት ተመልሷል ቢባልም፣ በአጋዥ መተግበሪያዎች የሚሠራ እንጂ፣ ራሱን ችሎ የሚያስጠቅም አለመኾኑን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም፣ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለጥቅል አገልግሎት የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን ተከትሎ፣ የዓመት ቅድሚያ ክፍያ መክፈላቸውን ያወሱት ነዋሪዎቹ፣ ቴሌ፣ አገልግሎት ላላገኙባቸው ወራት ማካካሻ እንዲደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በዚኽ ሳምንት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀርበው ሪፖርት፣ በአገሪቱ ያለው የማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ ዘዴዎች እገዳ መቀጠሉ አሳስቦታል፡፡

በነዋሪዎች በተነሡት ቅሬታዎች ላይ መረጃ ለማግኘት፣ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራሮች የእጅ ስልክ ላይ ደጋግመን ብንደውልም፣ ጥሪው ምላሽ ባለማግኘቱ አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡

XS
SM
MD
LG