በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲጂታል የነዳጅ ግብይት መጀመሩ በማደያዎች መጨናነቅን ፈጥሯል


ዲጂታል የነዳጅ ግብይት መጀመሩ በማደያዎች መጨናነቅን ፈጥሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:43 0:00

ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በዲጂታል የክፍያ ስርዐት እየተከናወነ ያለው የነዳጅ ግብይት፣ በዐዲስ አበባ ማደያዎች ከፍተኛ መጨናነቅን በመፍጠሩ ለሥራ ሰዓት ብክነት እንደዳረጋቸው አሽከርካሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡

ችግሩ በከተማዋ የትራንስፖርት መስተጓጎል እንደፈጠረም አሽከርካሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ በማደያዎች ነዳጅ ለመቅዳት ከአንድ ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ድረስ ተራ በመጠበቅ እያሳለፉ እንደሆኑ የተገለፁት እነዚሁ አስተያየት ሰጭዎች፣ በአዲሱ አሰራር ዙርያ ያለው ግንዛቤ አናሳ መኾን ችግሩን እንደፈጠረው አመልክተዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ዙርያ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጠው ኢትዮ-ቴሌኮም፣ ግንዛቤው የሌላቸውን ደንበኞች ለማገዝ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልፆ፣ የግብይት መዘግየት ሁኔታው ከማደያዎች አቅም ጋር የሚያያዝ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

የነዳጅ ማደያ ሠራተኞች ደግሞ በሥራ ላይ የዋለው ዲጂታል የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ እንዲህ ዓይነት ችግር እንዳይፈጥር በአንዴ ሳይሆን በሒደት መተግበር እንደነበረበት ተናግረዋል፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በበኩሉ ደንበኞች ለዝግጅት የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ አለመጠቀማቸው፣ በማደያዎች የሚታየው መጨናነቅ እንዲፈጠር አስተዋፅኦ አድርጓል በማለት ለመንግስት ብዙሃን መገናኛ ገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG