በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
አፍሪካ ኅብረት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለፕሪቶሪያው ስምምነት ተፈጻሚነት ትኩረት እንዲሰጡ ትግራይ ክልል ጥሪ አቀረበ

አፍሪካ ኅብረት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለፕሪቶሪያው ስምምነት ተፈጻሚነት ትኩረት እንዲሰጡ ትግራይ ክልል ጥሪ አቀረበ


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌላኛውን የህወሓት ቡድን የሚመሩት ዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ተገኝተዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌላኛውን የህወሓት ቡድን የሚመሩት ዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ተገኝተዋል።

ትግራይ ክልል ይኽን ጥሪ ያቀረበው፣ አዲስ አበባ ላይ ሲካሔድ የቆየው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ማጠናቀቂያ ቀን፣ በፕሪቶሪያ የተደረሰው በዘላቂነት ተኩስ የማቆም የሰላም ስምምነት በተመለከተ ለጋዜጠኞች በተሰጠ የማብራሪያ ሪፖርት ላይ ነው።

የፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ ያተኮረው ሪፖርት፣ ከመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ሲካሔድ ፣አጠቃላይ ሂደቱና ተገኝተዋል የተባሉ ትምሕርቶችን የተመለከተ ሪፖርት ይፋ ተደርጓል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌላኛውን የህወሓት ቡድንን የሚመሩት ዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ተገኝተዋል። ሁለቱ መሪዎች የእጅ ሰላምታ ተሰጣጥተውና ጎን ለጎን ተቀምጠው ተቀምጠው ማብራሪያና ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች፣ እንዲሁም ዋና አደራዳሪ የነበሩትን ኦሉሴጉን ኦባሳንጆን አና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓ መካከል ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በፕሪቶሪያ የተደረሰው በዘላቂነት ተኩስ የማቆም የሰላም ስምምነት በአፍሪካ ኅብረት መሪነት እውን የኾነ የመጀመሪያው ውጤታማ ተብሎ የሚጠቀስ የሰላም ስምምነት ነው፡፡
በሪፖርቱ ላይ መነሻውን በትግራይ ክልል አድርጎ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተስፋፋው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ ከተቀሰቀሰ ከአንድ ዓመት በኋላ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን፣ የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የኅብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ በማድረግ ለግጭቱ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ በመሾም ግጭቱን በሰላም ለማስቆም ከተለያዩ አካላት ጋራ ያደረጋቸውን ጥረቶች ተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች ቀርበዋል፡፡

የሰላም ስምምነቱ ዋና አደራዳሪ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ፣ የትግራይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌላኛውን የህወሓት ቡድን የሚመሩት ዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል እጆች ይዘው ሲያነጋግሯቸው።
የሰላም ስምምነቱ ዋና አደራዳሪ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ፣ የትግራይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌላኛውን የህወሓት ቡድን የሚመሩት ዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል እጆች ይዘው ሲያነጋግሯቸው።

በአፍሪካ ኅብረት በነበረው በዚህ ዝግጅት ላይ ንግግር ካደረጉ አካላት መካከል የሆኑት ተሰናባቹ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት፣ “ይህ ሪፖርት በመላው አፍሪካ ሰላምን ለማስፈን ለምናደርገው ጥረት መማሪያ የሚኾነን ነው” ብለዋል፡፡
የፕሪቶሪያው የሰላም ሂደት “ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” የሚለውን መርህ አጉልቶ የሚያሳይ ነው” ያሉት ዋና አደራዳሪው የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በበኩላቸው፣ “አፍሪካዊ ተቋማት በአህጉሪቱ ያሉ ግጭቶችን መፍታት እና ሰላም ማውረድ እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ህወሃትን በመወከል ስምምነቱን የፈረሙት የአሁኑ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፣ “ብዙ የስምምነቱ ይዘቶች አልተፈጸሙም” በማለት፣ የአፍሪካ ኅብረት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ “አልተፈፀሙም” ባሏቸው ነጥቦች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
ከእነዚኽም መካከል የተፈናቃዮች ጉዳይ እና የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተን እና ወደ ማኅበረሰቡ መልሶ ማዋሃድ (ዲዲአር) እንደሚገኙበት በአጽንኦት ገልፀዋል፡፡

ተሰናባቹ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት፣ “ይህ ሪፖርት በመላው አፍሪካ ሰላምን ለማስፈን ለምናደርገው ጥረት መማሪያ የሚኾነን ነው” ብለዋል፡፡
ተሰናባቹ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት፣ “ይህ ሪፖርት በመላው አፍሪካ ሰላምን ለማስፈን ለምናደርገው ጥረት መማሪያ የሚኾነን ነው” ብለዋል፡፡

"ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት የሚያደርገው በትጥቅ ማስፈታት ጉዳይ ላይ ብቻ ነው" ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ነገር ግን እነዚህን ታጣቂዎች መልሶ የማቋቋም ጉዳይም አብሮ የሚሄድ ጉዳይ መሆኑ መዘንጋት የለበትም ብለዋል፡፡
አሁን እዚህ እየተናገርን ባለንበት ወቅት “በርካታ ሴቶች እና ህፃናት በመጠለያዎች በስቃይ ላይ ይገኛሉ” በማለት፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች “በሕገመንግሥቱ የትግራይ አካል ወደሆኑ ወሰኖች የመመለሳቸው ጉዳይ” በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና በአፍሪካ ኅብረት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያን መንግሥት በመወከል በፕሪቶሪያው ድርድር ከተሳተፉት ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት አሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትረ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ስምምነቱን ለመፈፀም የሚያስችሉ ርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ ያልተፈፀሙ የሰምምነቱ ነጥቦች ደግሞ “በንግግር እና ሕግን ባከበረ መልኩ መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡
የሰላም ስምምነቱን በዋና አደራዳሪነት የመሩት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦባሳንጆ፣ የዲዲአር እና የአወዛጋቢ ቦታዎች ጉዳይ መፍትሔ እስኪያገኙ ድረስ በይደር መታየት እንዳለባቸው ገልፀው “የስምምነቱን ተፈጻሚነት ሊጎዱ እና ወደ ኋላ ሊመልሱት አይገባም” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG