በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቲክ ቶክ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አገልግሎት መስጠት አቆመ

ፎቶ ፋይል - የቲክ ቶክ አርማ በተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ በኮምፒዩተር ስክሪን ፊት ለፊት የቲክ ቶክ መነሻ ገጽ። በቦስተን፣ ማሳቹሴትስ ውስጥ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር መጋቢት 18/2023 ዓ.ም.
ፎቶ ፋይል - የቲክ ቶክ አርማ በተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ በኮምፒዩተር ስክሪን ፊት ለፊት የቲክ ቶክ መነሻ ገጽ። በቦስተን፣ ማሳቹሴትስ ውስጥ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር መጋቢት 18/2023 ዓ.ም.

ማኅበራዊ መገናኛው ቲክ ቶክ ከትላንት ቅዳሜ ማታ ጀምሮ በዩናይትድ ስቴትስ አገልግሎት መስጠት አቁሟል። አሜሪካ ውስጥ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክቶክ ከአፕል እና ጉግል መተግበሪያዎች የተነሳው አገልግሎቱ እንዲቆም የወጣው ሕግ በዕቅዱ መሠረት ዛሬ ዕሁድ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ነው።

ትላንት ቀደም ብሎ ተመራጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ነገ አስተዳደራቸውን ሲጀምሩ እገዳው ተግባራዊ እንዳይሆን ለቲክቶክ የሦስት ወር ጊዜ ሳልሰጥ አልቀርም ያሉ ሲሆን ቲክ ቶክ ለደምበኞቹ በወጣው ማሳሰቢያ ላይ ጠቅሶታል።

የቻይና ባይትዳንስ ኩባኒያ ንብረት የሆነው ቲክቶክ አሜሪካ ውስጥ ላሉት ተጠቃሚዎቹ ወደመተግበሪያው ለመግባት ሲሞክሩ አገልግሎቱ መቋረጡን ያስታወቀው ትላንት ማታ ለአምስት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ላይ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG