ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የተመዘገበው የጥምቀት በዓል ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በድምቀት ተከብሯል። በዓል ከሚከበርባቸው ቀደምት ቦታዎች አንዱ ጃን ሜዳ ሲኾን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተገኙበት፣ የጥምቀት ሥነ-ስርዐቱ ተከናውኗል፡፡
ፓትሪያርኩ በንግግራቸው፣ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል። የእምነቱ ተከታዮች እና ጎብኚዎችም አስተያየት ሰጥተውናል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም