በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን ተቆጣጥራው የነበረውን የሩሲያ ክፍል አርባ ከመቶ አጣች


የዩክሬን ወታደሮች በቀብር ስነስርዓት ላይ
የዩክሬን ወታደሮች በቀብር ስነስርዓት ላይ

ዩክሬን ባለፈው ነሀሴ ወር 2016 ዓ.ም ላይ በድንገተኛ ወረራ ተቆጣጥራ የነበረውን የሩስያ ኩርስክ ግዛት ከ40 ከመቶ በላይ በላይ አጥታለች በማለት የዩክሬን ከፍተኛ ወታደራዊ ምንጭ አስታወቀ።

የዩክሬን ጄኔራሎች ባልደረባ የሆኑት የመረጃ ምንጩ፣ የዩክሬን ኃይሎች ባለፈው ነሀሴ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ሩሲያ ሰርገው ከገቡ በኋላ፤ ሩሲያ 59 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮቿን ወደ ኩርስክ ክልል አሰማርታለች ብሏል። ሩሲያ ዩክሬንን ሙሉ በሙሉ መውረር ከጀመረች ሁለት ዓመት ተኩል ሆኗታል።

በወቅቱ "1,376 ስኩዌር ኪሎ ሜትር አካባቢ ተቆጣጥረን ነበር” ያሉት የዩክሬን መረጃ ምንጩ፤ አያይዘውም “ይሁን እንጂ አሁን ላይ ጠላት የመልሶ ማጥቃት እርምጃውን እየጨመረ ነው" ብለዋል። የመረጃ ምንጩ በአሁን ሰዓት ዩክሬን በግምት 800 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሆን የሩሲያን ግዛት በቁጥጥሯ ስር ማዋሏን በመግለጽ “ይህንን ግዛት ወታደራዊ አግባብ እስከሆነ ድረስ እንይዛለን” በማለት ተናግረዋል።

የዩክሬን ወታደራዊ ምንጩ አከለውም 11 ሺህ የሚጠጉ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩሲያን ለመደገፍ ወደ ኩርስክ ክልል መግባታቸውን ገልጿል። ነገር ግን አብዛኛው ሰራዊታቸው ገና ስልጠናቸውን እያጠናቀቁ ነው ብሏል።

ኪቭ በኩርስክ ክልል ስላለው የወታደራዊ ሁኔታ አስተያየት እንድትሰጥ በሮይተርስ ለቀረበለው ጥያቄ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም። ሮይተርስ በዩክሬን ወታደራዊ የመረጃ ምንጭ የተገለሱት አሃዞች እና መግለጫዎች እውነተኛነት በራሱ ማረጋገጥ አለመቻሉን ዘግቧል። ይሁን እንጂ ሩሲያ የሰሜን ኮሪያ ጦር በኩርስክ መገኘቱን አላረጋገጠም ወይም አልካደችም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG