በናይጄሪያ ሳምንታት የዘለቀው ጎርፍ 185 ሰዎችን ሲገድል እጅግ ብዙ የእርሻ ቦታዎችን እና የመኖሪያ ቤቶችን አውድሟል።
የሀገሪቱ የአደጋ ዝግጁነት ተቋም ጎርፉ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰበት በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ላይ ተጨማሪ የምግብ አቅርቦት ስጋትን ጥሏል ሲል አስታውቋል።
በአግባቡ ጥገና ባልተደረገለት ግድብ እና በደካማ መሰረተ ልማት ምክንያት የተከሰተው ጎርፍ 208,000 ሰዎችን ያፈናቀለ ሲሆን ከ36 ግዛቶች 28 ውስጥ ጉዳት አድርሷል፤ ሲል የናይጄሪያ የአደጋ ቁጥጥር ተቋም አርብ ዕለት አስታውቋል።
በተጨማሪም ጎርፉ የሀገሪቱ ምግብ በሚመረትበት ሰሜናዊ ክልል 107 ሺህ ሄክታር የእርሻ መሬትን አውድሟል።
አብዛኞቹ የአካባቢው ገበሬዎችም በጎርፉ ምክንያት ሰብል ማምረት አለመቻላቸውን አስታውቀዋል። ናይጄሪያ በአለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በአጣዳፊ ርሃብ የተጎዱ ህዝቦች ያሏት ሀገር ስትሆን፤ የመንግስታቱ ድርጅት የምግብ ተቋም ሀገሪቱ የአለም የርሃብ ሽክምን አስር ከመቶ እንደያዘች አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም