በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልስጤማውያን በእስራኤል የአየር ጥቃት ለተገደሉት ሀዘናቸውን እየገለጹ ነው


ፎቶ ኤኤፍፒ (መጋቢት 15፣2024)
ፎቶ ኤኤፍፒ (መጋቢት 15፣2024)

ፍልስጤማውያን ሀዘንተኞች፣ በጋዛ ከተሞች በሚገኙ ሦስት የስደተኛ መጠለያ ካምፖች በእስራኤል የአየር ጥቃት የተገደሉ 30 ሰዎችን ዛሬ ረቡዕ ማዕከላዊ ጋዛ የሚገኝ ሆስፒታል ደጃፍ ተሰብስበው በጸሎት ሸኝተዋል፡፡

የሟቾቹ አስክሬን በአህዮች በሚጎተቱ ጋሪዎች ተጭኖ ለቀብር ከመወሰዱ በፊት ሀዘንተኞቹ በተሸፈኑት አስከሬኖች ላይ ተደፍተው ሲጸልዩ አሶሴይትድ ፕሬስ የቀረጸው የቪዲዮ ምስል አሳይቷል፡፡

ትላንት ማክሰኞ ማምሻው ላይ ከተማው ውስጥ በሚገኝ ኑሴይራት የስደተኞች መጠላይ ካምፕ ውስጥ የነበረውን የቤተሰብ መኖሪያ ቤት ባወደመው የአየር ጥቃት አምስት ሴቶች እና ዘጠኝ ህጻናትን ጨምሮ 19 ሰዎች ተገድለዋል።

በካምፑ ውስጥ በተፈፀመ ሌላ የአየር ጥቃት አንድ ሌላም ሰው ተገድሏል።

በአቅራቢያው በሚገኘው የቡሬጅ መጠለያ ካምፕ በደረሰ ሌላም ጥቃት እንዲሁ ሶስት ሴቶችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች ተገድለዋል፡፡

አስክሬኖቹ በማዕከላዊ ጋዛ ዋነኛው የሕክምና ተቋም ወደሆነው ወደ አል-አቅሳ ሰማዕታት ሆስፒታል መወሰዳቸውን የዘገበው የአሶይትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ አስከሬኖቹ ገብተው ስማቸው በሆስፒታሉ መዛግብት ሲሰፍር መመልክቱን ገልጿል።

ኑሴይራት እና ቡሬጅ ከአሁኒቷ እስራኤል አመሰራረት ጋር ተያይዞ ከተነሳው ጦርነት በመሸሽ፣ እ አ አ በ1948 ወደ 700,000 የሚገመቱ ፍልስጥኤማውያን ስደተኞች ከቤት ንብረታቸው ከተፈናቀሉበት ጊዜ ጀምሮ፣ ስደተኞች ጥቅጥቅ ብለው ከሚኖሩባቸው በርካታ የመጠለያ ካምፖች መካከል የሚገኙ ናቸው፡፡

ዛሬ 2.3 ሚሊዮን ከሚሆነው የጋዛ ህዝብ አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት እነዚያ ቀደምቶቹ ፍልሰተኞችና ተወላጆቻቸው መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG