በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ ጊዜያዊ ወደብ ለመገንባት አሜሪካ መሣሪያዎችን ላከች


ወደ ቀይ ባሕር ያቀናችው የአሜሪካ ወታደራዊ መርከብ ከቨርጂኒያ ትናንት ቅዳሜ ከመነሳቷ በፊት ያሳያል (ፎቶ ኤፒ መጋቢት 10፣ 2024)
ወደ ቀይ ባሕር ያቀናችው የአሜሪካ ወታደራዊ መርከብ ከቨርጂኒያ ትናንት ቅዳሜ ከመነሳቷ በፊት ያሳያል (ፎቶ ኤፒ መጋቢት 10፣ 2024)

በጋዛ ግዜያዊ ወደብ ለመገንባት የሚያስፍልጉ መሣሪያዎችን የተሸከመ የአሜሪካ ወታደራዊ መርከብ ወደ ሜዲትሬንያን ባሕር በማቅናት ላይ ይገኛል።

መርከቧ ወደ ቀጠናው ያቀናቸው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በጋዛ ሰርጥ በከበባ ውስጥ ለሚገኙና በረሃብ ላይ ላሉ በመቶ ሺሕ ለሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በባሕር በኩል ዕርዳታ እንዲደርሳቸው እንዲደረግ ባሳሰቡ በሁለት ቀናት ውስጥ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል በጋዛ በሚገኘው ሐማስ ላይ የምታካሄደው ጦርነት ቀጥሏል። ዛሬ ሌሊት ቢያንስ 22 የሚሆኑ ፍልስጤማውያን በእስራኤል የአየር ድብደባ እንደተገደሉ ታውቋል።ከሟቾቹ ውስጥ ሕፃናትና ሴቶች እንዲሁም አንድ አራስ ሕጻን እንደሚገኙበት ታውቋል።

ፕሬዝደንት ባይደን እስራኤል ጦርነቱን የምታካሂድበትን መንገድ በጽኑ ነቅፈዋል። እስራኤል የሲቪሎችን ግድያ ለማስቆም ተጨማሪ ጥረት እንድታደርግ ጠይቀዋል።

በጋዛ ዕርዳታ ለማድረስ የባሕር በር መከፈቱ እንዲሁም አሜሪካ፣ ጆርዳን እና ሌሎችም አገራት ከአየር ምግብ ልመጣል መገደዳቸው፣ በጋዛ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ እንዲሁም አገራቱ እስራኤል በምድር የምትቆጣጠረውን የዕርዳታ ስርጭት ለመተው ማሰባቸውን ያመለከተ ነው ተብሏል።

በባሕር ሊደረግ የታቀደውን ዕርዳታ እስራኤል በመልካም እንደምታየው ገልጻ፣ ወደ ጋዛ የሚላከውን ጭነት ግን በአቅራቢያው ከምትገኘው ቆጵሮስ ከመነሳቱ በፊት እንደምትፈትሽ አስታውቃለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG